Fana: At a Speed of Life!

ታንዛኒያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ክፍ ወዳለ ደረጃ ለማሳደግ ትሻለች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የታንዛኒያ መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ክፍ ወዳለ ደረጃ ለማድረስና የአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ትብብሩን የማሳደግ ፍላጎት እንዳለው በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙት የአገሪቱ አምባሳደር ኢኖሰንት ኡጉኒ ገለጹ።

አምባሳደሩ የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባቀረቡበት ወቅት የኘሮቶኮል ምክትል ሹሙ አምባሳደር አለማየሁ ሰዋአገኝ ባደረጉት ንግግር፥ ኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ የረጅም ጊዜ ወዳጅነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን አስታውሰዋል።

ዛሬም ድረስ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ጠንካራ ሆኖ መቀጠሉን ነው አምባሳደሩ የገለጹት።

በንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ቱሪዝም መስኮች ያላቸውን ግንኙነት ማጠናከር የኢትዮጵያ ፍላጎት መሆኑን ገልፀውላቸዋል።

በአባይ ውሃ ፍትሃዊ አጠቃቀም እንዲሰፍን እያራመደች ላለው አቋም ተገቢ መሆን የገለፁ ሲሆን ÷ ሁሉን አቀፍ የናይል አጠቃቀም ስምምነትን በመፈረም እና በማፅደቋም ምስጋና አቅርበዋል።

አዲስ ተሿሚው የታንዛኒያ አምባሳደር ኢኖሰንት ኡጉኒ በበኩላቸው ÷ የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማድረስ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በአየር ትራንስፓርት መስክ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በታንዛንያ ሶስት መዳረሻዎች እንዳለው ገልፀው ÷ የታንዛኒያ መንግስት በዘርፉ ያለውን ትብብር የማሳደግ ፍላጎት አለው ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የሀገራቱ አገራት ቀደምት መሪዎች አፄ ሃይለስላሴ እና ጁሊየስ ኔሬሬ ለአፍሪካ ህብረት መመስረት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸው ይታወሳል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.