Fana: At a Speed of Life!

ታንዛኒያ የሴካፋ ከ23 አመት በታች ዋንጫ አሸናፊ ሆነች

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በባህር ዳር ሲካሄድ የቆየው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ (ሴካፋ) ከ23 አመት በታች እግር ኳስ ውድድር በታንዛኒያ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

ዛሬ በፍጻሜ ጨዋታ ከብሩንዲ ጋር የተጫወተችው ታንዛኒያ በመለያ ፍጹም ቅጣት ምት አሸናፊ ሆናለች፡፡

መደበኛው የጨዋታው ክፍለ ጊዜ ያለምንም ጎል አቻ በሆነ ውጤት የተጠናቀቀ ሲሆን፥ በመለያ ፍጹም ቅጣት ምት ታንዛኒያ 6 ለ 5 አሸንፋለች፡፡

የኢትዮጵያው የአጥቂ መስመር ተጫዋች የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.