Fana: At a Speed of Life!

ትምህርት ቤት ለመሄድ በየቀኑ የሀገር ድንበር የሚያቋርጡት መንትዮች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2012 (ኤፍ. ቢ.ሲ) ትምህርት ቤት ለመሄድ በየቀኑ የሀገር ድንበር የሚያቋርጡት መንትያ እህቶች ብዙዎችን አስገርመዋል።

ከአንድ ሉዓላዊ ሀገር ወደ ሌላ ሀገር ለስራም ሆነ ለጉብኝት በሚኬድበት ጊዜ የተለያዩ ህጋዊ ሂደቶችን ማለፍ ግድ ነው።

አንድ ዜጋ ጎረቤት ወደ ሚገኝ ሀገር ለመግባት የሚያስፈልጉ መስፈርቶችን ካሟላ በኋላም ድንበር አካባቢ የተለያዩ የፍተሻ ሂደቶችን ማለፍ ይጠበቅበታል።

በዚህ ወቅትም በሀገሪቱ ድንበር ጠባቂዎች ተገቢ ያልሆነ መንገላታት እና ሰብዓዊ መብት ጥሰት ሊያጋጥም ይችላል።

አና ፈርናንዳ እና አና ሉዊዝ በርናል የተባሉ የ16 ዓመት መንትያ እህቶች ግን እንደሌሎች ለጉብኝት ሳይሆን ትምህርት ቤት ለመሄድ በየቀኑ የሀገር ድንበር ማቋረጥ ግድ ብሏቸዋል።

እህትማማቾቹ የተወለዱት አሜሪካ ሲሆን፥ የሚኖሩት ግን በእናታቸው ሀገር ሜክሲኮ ነው።

ይሁን እንጅ መንትዮቹ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት ለመማር ወደ ተወለዱበት ሀገር አሜሪካ መሄድ ይጠበቅባቸዋል።

የትምህርት ፍላጎታቸውን ለማሳካትም በየቀኑ ዓለም አቀፍ ድንበር ለማቋረጥ ተገደዋል።

በዚህ መሰረት ከመዋዕለ ህፃናት ጀምሮ እስከ 2ኛ ደረጃ ድረስ በየዕለቱ የአሜሪካን ድንበር በማቋረጥ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛል።

እንደማንኛውም የውጭ ሀገር ዜጋ ድንበር አካባቢ የሚያጋጥማቸውን የፍተሻ ስርዓት ለማለፍም በዕለቱ በጠዋት ከቤታቸው በመነሳት ወደ ስፍራው እንደሚያቀኑ ተገልጿል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.