Fana: At a Speed of Life!

ትራምፕ ምርጫው ተጭበርብሯል በሚል ያቀረቡት ክስ ውድቅ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ የፌደራል ምርጫ ባለስልጣናት የ2020 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በአሜሪካ ታሪክ ደህንነቱ በእጅጉ የተጠበቀ ምርጫ ነበር አሉ።

የምርጫ ባለስልጣናቱ  ዶናልድ ትራምፕ ምርጫው ተጭበርብሯል በማለት ያቀረቡትን አቤቱታ ውድቅ አድርገዋል።

የምርጫ ስርዓቱ መሰረዙን፣ የተሰወሩ ድምፆች መኖራቸውን፣ የድምፅ ለውጥ መኖሩን እና በማንኛውም መንገድ ምርጫውን ለማጭበርበር የተደረገ ስምምነት እንደነበር የሚያሳይ ማስረጃ አልተገኘምም ብለዋል።

ይህ የባለስልጣናቱ አስተያየት የተሰማው ዶናልድ ትራምፕ ያለምንም ማረጋገጫ 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ድምፅ ተሰርዟል ሲሉ ባለፈው ሳምንት ከተናገሩ በኋላ ነው።

በአሜሪካ የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ የምርጫ ሂደት የሚመራው አካል ይፋ ባያደርገውም ዓለም አቀፍ  መገናኛ ብዙሃን ጆ ባይደን ማሸነፋቸውን ገልፀዋል።

ነገር ግን ዶናልድ ትራምፕ ምርጫ መካሄድ ከመጀመሩ በፊትም ሆነ ከተካሄደ በኋላ ምርጫው መጭበርበሩን ሲገልፁ ቆይተዋል።

የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ደህንነት የሚቆጣጠረው የአሜሪካ የሀገር ውስጥ ደህንነት ዲፓርትመንት የጋራ መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫው የበይነ መረብ ደህንነት እና የመሰረተ ልማት ደህንነት ኤጀንሲ ኮሚቴ ÷ በምርጫ ሂደቱ  ላይ የተሳሳተ ግንዛቤ ሊፈጥሩ የሚችሉ እና  ያልተረጋገጡ ውሳኔዎች እንዳሉ መግለፁን ቢቢሲ ዘግቧል።

ኮሚቴው ማረጋገጥ የምንፈልገው በምርጫው ላይ የምንተማመንበት የደህንነት ስርዓት እና ታማኝነት አለን ነው ያለው በመግለጫው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.