Fana: At a Speed of Life!

ትራምፕ የሃገሪቱን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኦባማ ኬርን እንዲያቋርጥ ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሃገሪቱን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለበርካታ አሜሪካውያን የጤና መድህን ሽፋን የሚሰጠውን ኦባማ ኬር እንዲያቋርጥ ጠየቁ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ኦባማ ኬር ኢኒሼቲቭ መንግስትን ከፍተኛ ወጪ የሚያስወጣ ነው በማለት ፍርድ ቤቱ እንዲያቋርጥላቸው ጠይቀዋል ፡፡

በኦባማ ኬር ምትክም አዲስ የጤና መድህን ሽፋን አገልግሎት ለማዘጋጀት ማቀዳቸውን ተናግረዋል፡፡

የዴሞክራቱ ተቀናቃኛቸው ጆ ባይደን በበኩላቸው የትራምፕን ሃሳብ ኮንነዋል፡፡

እንደ እርሳቸው ገለጻ የትራምፕ እቅድ በሚሊየን የሚቆጠሩ የአሜሪካውያን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥል እና ያልተገባ ነው ፡፡

በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የተጀመረው ኦባማ ኬር ኢኒሼቲቭ ወደ 20 ሚሊየን ለሚጠጉ ሰዎች የጤና መድህን ሽፋን ይሰጣል፡፡

ፍርድ ቤቱ የትራምፕን ሃሳብ ቀብሎ የሚቋርጠው ከሆነ በጤና መድህን ሽፋኑ ተጠቃሚ የሆኑ 20 ሚሊየን ሰዎች ችግር ላይ ይወድቃሉ ነው የተባለው፡፡

ይህም ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተደምሮ ከፍተኛ የጤና ቀውስ ሊያስከትል እንደሚችል ነው የተገለጸው፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.