Fana: At a Speed of Life!

ትእምት (ኢፈርት) በጥቂቶች ተይዞ ቢቆይም የህዝብ ሃብት ስለሆነ ስራው እንዲቀጥል መንግስት መወሰኑን ዶ/ር አብርሃም በላይ አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ትእምት (ኢፈርት) ምንም እንኳ በጥቂቶች ተይዞ ቢቆይም የህዝብ ሃብት ስለሆነ ስራው እንዲቀጥል መንግስት መወሰኑን የትግራይ ብልፅግና ከፍተኛ አመራር ዶክተር አብርሃም በላይ አስታወቁ።
ዶክተር አብርሃም ዛሬ ለጋዜጠኞች በመቐለ ከተማ በሰጡት መግለጫ ÷ትእምት (ኢፈርት) በጥቂት የጁንታው አባላት ተይዞ ቆይቷል ብለዋል።
ይሁን እንጂ ተቋሙ የህዝብ ሃብት ስለሆነ ስራው እንዲቀጥል መንግስት ወስኗልም ነው ያሉት።
ዶክተር አብርሃም አያይዘውምበተቋሙ ላይ የተጀመረው የፍርድ ቤት ጉዳይ ጎን ጎን ይቀጥላል ብለዋል።
ከዚያም ባለፈ የትእምት ሰራተኞች ስራቸውን እንዲጀምሩ አቅጣጫ መቀመጡን ገልጸው÷አመራሩ በባለአደራ እንዲመራ መንግስት አምኖበት ለፍርድ ቤት ለውሳኔ አቅርቧል ነው ያሉት።
የባለ አደራ ቦርዱ 7 አባላት ያሉት ሲሆን 5ቱ በትምህርት እና በተመሳሳይ ዘርፍ ልምድ ያላቸው ናቸው መሆናቸውን ጠቁመው÷ሁለቱ ደግሞ ከገንዘብ እና ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የተመረጡ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የትእምት ጉዳይ በፍርድ ቤት የተያዘ ቢሆንም የተወረሰ ነገር የለም ያሉት ዶክተር አብረሃም ÷ የተቋሟቱ ሰራተኞች ደሞዝ እንዲከፈል እና ሰራተኞቹ ስራ እንዲጀምሩ መንግስት ወስኗል ብለዋል።
ከህግ ማስከበር ዘመቻው በተቃራኒ በመቆም በውግያ የተሳተፉ የተቋማቱ ተንቀሳቃሽ ንብረቶች ጉዳይም በህግ አግባብ ይታያል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.