Fana: At a Speed of Life!

ትዊተር ፕሬዚዳንት ትራምፕን በዘላቂነት አገደ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ትዊተር የአሜሪካውን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዘላቂነት ማገዱን አስታወቀ፡፡

ኩባንያው ፕሬዚዳንቱን ተጨማሪ የአመፅ ድርጊቶችን ሊቀሰቅስ ይችላሉ በሚል ስጋት ማህባረዊ የትስስር ገጹን እንዳይጠቀሙ ለዘለቄታው እንደከለከላቸው አስታውቋል፡፡

የትዊተር ኩባንያ ትራምፕ @realDonaldTrump በሚለው የትዊተር አካውንታቸው በቅርቡ ያሰፈሯቸውን መልዕክቶች ከመረመረ በኋላ ውሳኔ ማሳለፉንም ገልጿል፡፡

የአሁኑ እገዳ ትራምፕ ከካፒቶል ሒሉ ክስተት በኋላ በትዊተር ከተጣለባቸው እገዳ በኋላ ባሰራጯቸው መልዕክቶች አማካኝነት በቋሚነት የተጣለ መሆኑም ታውቋል፡፡

ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ረቡዕ ካፒቶል ሒልን የወረሩ ደጋፊዎቻቸውን “አርበኞች” ብለው ካሞገሱ በኋላ ለ12 ሰዓታት ትዊተር እንዳይጠቀሙ ታግደው እንደነበር ይታወሳል።

በወቅቱ የአሜሪካ ምክር ቤት አባላት የጆ ባይደንን የምርጫ ውጤት ለማረጋገጥ ስብሰባ ላይ ነበሩ፡፡

በዚህ ወቅትም የትራምፕ ደጋፊዎች ወደ ምክር ቤቱ ህንጻ በመግባት በፈጠሩት ግርግር አንድ የፖሊስ አባልን ጨምሮ የአምስት ሰዎች ህይወት አልፏል።

ትዊተርም ፕሬዚዳንቱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ደንቦች እንዳይጥሱና ይህን ካደረጉ እገዳ እንደሚጥል አስጠንቅቆ ነበር፡፡

ይሁን እንጅ በፕሬዚዳንቱ አካውንት ዳግም በተለጠፉ መልዕክቶች ሳቢያ እገዳው ተጥሎባቸዋል፡፡

አንዳንድ የአሜሪካ ሕግ አውጪዎች እና ታዋቂ ሰዎች ትራምፕ ከትዊተር እስከወዲያኛው እንዲታገዱ ሲወተውቱ ቆይተዋል፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.