Fana: At a Speed of Life!

ቻይና በምስራቅ አፍሪካ ልዩ መልዕክተኛ ትሾማለች – የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋንግ ዪ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና በምስራቅ አፍሪካ የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ልዩ መልዕክተኛ እንደምትሾም አስታወቀች፡፡

የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የቻይናው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በሀገራቱ የሁለትዮሽ እና ከሌሎች ሀገራት ጋር በሚያደርጓቸው ግንኙነቶች ላይ ተወያይተዋል፡፡

የሁለቱ ሀገራት ባለሥልጣናት እና የቻይና ልዑካን ቡድኖች በሀገራቱ መካከል በሚካሄዱ የልማት ትብብር ማዕቀፎች ፣ በቀጣናው በሚስተዋሉ የሠላምና ደኅንነት ሥጋቶች እንዲሁም ዓለም አቀፋዊ ወረርሽኝ የሆነውን የኮቪድ-19 ቫይረስ ሥርጭት ለመግታት በሚደረገው ጥረት ላይ ተወያይተዋል፡፡

የቻይናው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ የሀገሪቷን ንግድ ሚኒስቴር ኪያንግ ኬሚንክ፣ ረዳት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዉ ጂያንጋዎ እንዲሁም በኬንያ የቻይና አምባሳደር ዦው ፒንግ ጂያንግ ጋር በመሆን ኬንያ ያቀደቻቸውን የልማት አጀንዳዎች ለመፈጸም የምታደርገውን ጥረት ቻይና ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል፡፡

የቻይና የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋንግ ዪ ከኬንያ አቻቸው ጋር በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፥ ቻይና በምስራቅ አፍሪካ የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲሁም የቀጠናውን ዘላቂ ሠላምና ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ልዩ መልዕክተኛ ትሾማለች ማለታቸውን የዘገበው ሲጂቲ ኤን ነው፡፡

በኬንያው ፕሬዚዳንት እና በቻይና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር እና ልኡካን ቡድናቸው ውይይት ላይ የኬንያን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ራይቼል ኦማሞን ጨምሮ ሌሎች የኬንያ ጉምቱ የልማት ተቋማት ሃላፊዎች እንደተገኙ ነው የታወቀው፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.