Fana: At a Speed of Life!

ቻይና በቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮን ጨምሮ በ28 አሜሪካውያን ላይ ማዕቀብ ጣለች

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና በቀድሞው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮን ጨምሮ በ28 አሜሪካውያን ላይ ማዕቀብ ጣለች፡፡

ማዕቀቡ ግለሰቦቹ በቻይና የውስጥ ጉዳይ ላይ ገብተዋል በሚል የተጣለ መሆኑን የቻይና ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታውቋል፡፡

የትራምፕ የንግድ አማካሪ ፒተር ናቫሮ፣ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሮበርት ኦብሪየን፣ የምስራቅ እስያ እና የፓሲፊክ ጉዳዮች ረዳት ፀሃፊ ዴቪድ እስቲልዌል፣ የጤና ሚኒስትሩ አሌክስ አዛር፣ በተመድ የአሜሪካ ልዑክ ኬሊ ክራፍት፣ የቀድሞው የትራምፕ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ጆን ቦልተን እና የቀድሞው አማካሪ ስቴፈን ባኖን ላይ ማዕቀብ መጣሏ ተገልጿል፡፡

ሚኒስቴሩ ማዕቀብ የተጣለባቸው የቀድሞ የስራ ሃላፊዎች ከራስ ወዳድ የፖለቲካ ፍላጎቶቻቸው እና ለቻይና ያላቸው ጥላቻ፥ ለቻይና እና ለአሜሪካ ህዝብ ፍላጎት ምንም ክብር እንደሌላቸው ያሳያልም ነው ያሉት ፡፡

የባይደን አስተዳደር የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት እርምጃውን “ፍሬያማ ያልሆነ እና ተንኮል የተሞላበት” ሲል ገልጾታል፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.