Fana: At a Speed of Life!

ቻይና በቁልፍ ጉዳዮች ላይ ከአሜሪካ ጋር ያላትን ትብብር ማቋረጧን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ከአሜሪካ ጋር በተለያዩ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ የነበራትን ትብብር ማቋረጧን አስታውቃለች፡፡
 
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ÷ እርምጃው የአሜሪካ የአሜሪካ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ “የአንድ ቻይና መርህን” በመጣስ በታይዋን ጉብኝት ማድረጋቸውን ተከትሎ የተወሰደ መሆኑን ገልጿል፡፡
 
በውሳኔው መሰረትም ቻይና ከአሜሪካ ጋር በአየር ንብር ለውጥ፣ በወታደራዊ ጉዳዮች፣ ዓለም አቀፍ ወንጀለኞችን በጋራ መዋጋትን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ላይ የነበራትን ትብብር ማቋረጧን ነው ያስታወቀችው፡፡
 
በሁለቱ አገራት ወታደራዊ ባለስልጣናት መካከል የሚካሄደው የጋራ ውይይት የሚቋረጥ መሆኑም ተጠቅሷል።
 
ቤጂንግ የናንሲ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት የቻይናን ሉዓላዊነት የሚዳፈር ነው በሚል በአፈ ጉባኤዋ እና ቤተቦቻቸው ላይ ማዕቀብ መጣሏም ተመላክቷል፡፡
 
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ቢሊንከን በበኩላቸው ዛሬ በሰጡት አስተያየት÷ ቻይና ከዋሽንግተን ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ያላትን ግንኙነት ለማቋረጥ ያሳለፈችው ውሳኔ ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው ብለዋል፡
 
ውሳኔው÷ቻይና የታይዋንን ጉዳይ በውይይት ከመፍታት ይልቅ ኃይልን ለመጠቀም ማቀዷን እንደሚያመላክት መግለጻቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
 
ቻይና በተለይም በአየር ንብረት ለውጥ እና በሌሎች ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር አልሰራም ማለቷ አሜሪካን ሳይሆን ዓለምን እንደሚጎዳ ነው የገለጹት፡፡
 
በአንጻሩ አሜሪካ ከቻይና ጋር ያላት የሁለትዮሽ ግንኙነት ብሔራዊ ጥቅሟም ባስከበረ መልኩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥረት እንደምታደርግ ተናግረዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.