Fana: At a Speed of Life!

ቻይና በታይዋን የባህር ዳርቻዎች ላይ የተሳካ የሚሳኤል ጥቃት መፈጸሟን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና የወታደራዊ ልምምዴ አንድ አካል ነው ያለቸውን የሚሳኤል ጥቃት በታይዋን የባህር ዳርቻ ላይ መፈጸሟን አስታወቀች፡፡

የቻይና ጦር ምስራቃዊ ዕዝ አዛዥ እንደገለጹት÷የሀገሪቱ የተቀናጀ ወታደራዊ ሃይል በታይዋን የባህር ወሽመጥ ምስራቃዊ ክፍል የረጀም ርቀት የተኩስ ልምምድ አድርጓል፡፡

በዚህም በታይዋን ምስራቃዊ ክፍል በሚገኙ የባህር ዳርቻዎች ላይ የተሳካ የሚሳኤል ጥቃት መፈጸም መቻሉን ነው የገለጹት፡፡

ቻይና ቀደም ሲል የአንድ ቻይና ፖሊሲ በአሜሪካ መጣሱን ተከትሎ ወታደራዊ ምላሽ ለመስጠት በታይዋን ዙሪያ በባህር ኃይል፣ በአየር ሃይል እና በሌሎች ወታደራዊ  ክፍሎች ልምምድ ማድረግ መጀመሯን ሲጂቲኤን በዘገባው አስታውሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.