Fana: At a Speed of Life!

ቻይና በፈረንጆቹ 2028 የመጀመሪያውን የጠፈር የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ልትገነባ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና በፈረንጆቹ 2028 የመጀመሪያውን የጠፈር የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለመገንባት ማቀዷን አስታወቀች።
የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ጣቢውን በህዋ ላይ ለመገንባት የሚያስችል ደረጃ ላይ መድረሷን የቻይና የሕዋ አካዳሚ ቴክኖሎጅ አስታውቋል።
በሕዋ ላይ ያለውን የፀሐይ ብርሃን ወደ ኤሌክትሪክ ሐይል በመቀየርና ሳተላይቶችን በምህዋሩ በማሽከርከር ኃይልን ወደ ምድር ለማስተላለፍ መታቀዱንም ነው ያስታወቀው።
ይህ የፀሐይ ብርሃን ከከባቢ አየር ውጭ የበለጠ ብሩህ እንደመሆኑ መጠን ቀኑን ሙሉ ማለት በሚቻል ደረጃ እንደሚያበራም ተገልጿል።
የዢዲያን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ ቡድን በዚህ ወር ለሕዋ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የመጀመሪያውን “ፀሐይን ማሳደድ” በመባል የሚታወቅ ፕሮጀክት ሙከራ ማድረጉን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.