Fana: At a Speed of Life!

ቻይና አንበጣን ለመከላከል የሚረዱ ቁሳቁሶችን ለኢትዮጵያ አበረከተች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይና መንግስት አንበጣን ለመከላከል የሚረዱ ቁሳቁሶችን ለግብርና ሚኒስቴር አበረከተ፡፡

ከአንበጣ መከላከያ በተጨማሪ ፀረ-ተዋህስያን፣ መርጫ ቁሳቁሶች እና ርጭት በሚካሄድበት ወቅት የሚከላከሉ ቁሳቁሶች ተበርክተዋል፡፡

በርክክቡ ወቅት የግብርና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ማንደፍሮ ንጉሴ የቻይና መንግስት የበረሃ አንበጣን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመከላከል የሚያስችል ድጋፍ ማበርከቱን ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም የኢትዮጵያ እና የቻይና መንግስታት በግብርናው ዘርፍ ረጅም ዓመታት ያስቆጠረ ወዳጅነት እንዳላቸውም ነው የተናገሩት፡፡

በመጨረሻም የቻይና መንግስት እያደረገ ከሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ የቁሳቁስ እና የምግብ እርዳታ በተጨማሪ ኢትዮጵያን በልማት ለማገዝ ቁርጠኛ መሆኑንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.