Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ኩባንያዎቿ በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ እንደምታበረታታ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቻይና አሁን ካሉት በተጨማሪ ሌሎች በሀገሪቱ የሚገኙ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ እንደምታበረታታ  የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለፁ።

በቻይና ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ልዩ መልእክተኛ እና የኢፌዴሪ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ከቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ጋር በቤጂንግ ተወያይተዋል።

በውይይት ወቅትም የቻንያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ፥ ሁለቱ ሀገራት በፖለቲካው ዘፍር ያለዓቸውን ትብብር ለማጎልበት መስራት እንደሚጠበቅ እና የሀገራቱን ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ ለመደጋገፍ እንደሚሰራም አስታውቀዋል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን መጠነ ሰፊ ትብብር የበለጠ ለማጠናከርም ቻይና በርካታ ኩባንያዎቿ በኢትዮጵያ በመሰረተ ልማት ግንባታ እና በሌሎች ዘርፎች ኢንቨስት እንዲያደርጉ አስፈላጊትን ድጋፍ እና ትበብር እንደምታደርግላቸውም የውጭ ጉዳይ ሚኒስሩ አስታውቀዋል።

በሁለትዮሽ፣ በቀጠናዊ እና በዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይም የሁለቱን ሀገራት እንዲሁም የታዳጊ ሀገራትን ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ በጋራ የሚሰራው ስራ እንደሚጠናከርም አስታውቀዋል።

ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በቻይና ቆይታቸው ከሌሎች የቻይና የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ጋር የሁለቱን ሀገራት ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ xinhuanet.com

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.