Fana: At a Speed of Life!

ቻይና የሁለት ልጅ ፖሊሲዋን ልታነሳ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና በቤተሰብ ምጣኔ ላይ ትተገብረው የነበረውን የሁለት ልጅ ፖሊሲ ልታሻሽል ነው፡፡

የመንግስት ባለስልጣናትን ዋቢ ያደረገው የሺንዋ ዘገባ መንግስት ጥንዶች ሶስት ልጆችን እንዲወልዱ ሊፈቅድ መሆኑን ያመላክታል፡፡

መንግስት ከዚህ በፊት ጥንዶች ሁለት ልጆች ብቻ እንዲኖራቸው የሚያስገድድውን ፖሊሲ ተግባራዊ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

አሁን ላይም ይህን ፖሊሲ በመቀየር ጥንዶች ሶስት ልጆችን እንዲወልዱ የሚፈቅደው የውሳኔ ሃሳብ በሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ መጽደቁን ዘገባው አመላክቷል፡፡

የአሁኑ ውሳኔ ባለፉት አስር አመታት በተደረገ የዳሰሳ ጥናት የሃገሪቱ የህዝብ እድገት በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉን ተከትሎ የመጣ ነው ተብሏል፡፡

አሁን ላይ በሃገሪቱ ያለው የውልደት ምጣኔ ከ1960ዎቹ ወዲህ ዝቅተኛ መሆኑም ነው የተነገረው፡፡

ባለፈው አመት የተደረገ ጥናትም በቻይና 12 ሚሊየን ህጻናት መወለዳቸውን ያመላክታል፤ ይህም በፈረንጆቹ 2016 ከተወለዱት 18 ሚሊየን ህጻናት አንጻር በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል፡፡

ቻይና በፈረንጆቹ 1979 የህዝብ ቁጥሯን ለመቀነስ በሚል የአንድ ልጅ ፖሊሲን ያስተዋወቀች ሲሆን በፈረንጆቹ 2016 ደግሞ ፖሊሲዋን ቀይራ የሁለት ልጅ ፖሊሲን አስተዋውቃ ነበር፡፡

ከዚያን ጊዜ ወዲህም ፖሊሲው የማይተገብሩ ጥንዶች አስገዳጅ ውርጃን ጨምሮ ከስራ የመሰናበት እርምጃ ይወሰድባቸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.