Fana: At a Speed of Life!

ቻይና የሩሲያ ጦር “የጦር ወንጀል” መፈጸም አለመፈጸሙን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ምርመራ ተቃወመች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት የሩሲያ ጦር በዩክሬን ንጹሀን ላይ “የጦር ወንጀል” መፈጸም አለመፈጸሙን ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ምርመራ በመቃወም ድምጽ ሰጥታለች።

ምክርቤቱ የጦር ወንጀሎች ምርመራ እንዲፈቀድ የሚጠይቀውን የውሰኔ ሀሳብ በትናንትናው ዕለት በአብላጫ ድምጽ አጸድቋል፡፡

ቻይና ከዚህ ቀደም የሩሲያ- ዩክሬን ጦርነትን አስመልክቶ በምክርቤቱ በሚሰጡ ውሳኔዎች ላይ ድምጸ ተአቅቦ ስታደርግ እንደቆየች የጠቀሰው ዘገባው፥ በምክርቤቱ የሚደረገው ምርመራ ፖለቲካዊ አጀንዳ ያለው ነው በሚል የቀድሞ አቋሟን ቀይራ ተቃውሞ ማቅረቧ ተሰምቷል፡፡

በጄኔቫ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የቻይና ዲፕሎማት ቼን ሹ ጉዳዩን አስመልክተው እንዳሉት፥ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በምክርቤቱ የሚንጸባረቀው ፖለቲካዊ ፍላጎት እና ግጭት ከጊዜ ወደጊዜ እየተበራከተ ነው።

ይህም የምክርቤቱን ተዓማኒነት፣ገለልተኝነት እና አብሮነት በእጅጉ ጎድቷታል ብለዋል።

የጦር ወንጀሎች ምርመራ እንዲፈቀድ የሚጠይቀው ውሳኔ በምክርቤቱ በ33 ድጋፍ፣ በ12 ድምፀ ተአቅቦ እና በ2 ተቃውሞ መጽደቁን አር ቲ ዘግቧል፡፡

ከቻይና በተጨማሪ ኤርትራ የምክር ቤቱን ውሳኔ ስትቃወም፥ አርሜኒያ፣ ቦሊቪያ፣ ካሜሩን፣ ኩባ፣ ህንድ፣ ካዛኪስታን፣ ናሚቢያ፣ ፓኪስታን፣ ሴኔጋል፣ ሱዳን፣ ኡዝቤኪስታን እና ቬኒዙዌላ ደግሞ ድምጸ ተዓቅቦ አድርገዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.