Fana: At a Speed of Life!

ቻይና የክረምቱን የቤጂንግ ኦሎምፒክ ጨዋታ ለመዘገብ የሚመጡ ሚዲያዎችን በደስታ እንደምትቀበል ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና የቤጂንግ የክረምት ኦሎምፒክ ጨዋታዎችን ሊዘግቡ ከተለያዩ ሀገራት የሚመጡ ሚዲያዎችን በደስታ እንደምትቀበል የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን ገለጹ፡፡

ገንቢ ሀሳቦችን የሚያቀርቡ ጋዜጠኞችን ቻይና የምታበረታታ ሲሆን፥ ነገር ግን በፕሬስ ነፃነት ሰበብ የሀሰት ዜናዎችን እና መረጃዎችን በማስተላለፍ ሀገሪቱን እና የክረምት ኦሎምፒኩን ለማጥላላት ለሚመጡ የሚዲያ አካላት ቦታ እንደሌላት ቃል አቀባዩ ዋንግ ዌንቢን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

የቻይና ቤጂንግ የክረምት ኦሎምፒክ ጨዋታን ለመዘገብ 2 ሺህ 500 የሚደርሱ በተለያዩ አለማት የሚኖሩ ጋዜጠኞች እና ፎቶግራፍ አንሺዎች ጥያቄ ማቅረባቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

ጨዋታው በፈረንጆች አቆጣጠር ከየካቲት 4/ 2022 እስከ የካቲት 20 /2022 እንደሚካሄድ ይታወቃል፡፡

የቻይናዋ ቤጂንግ ከተማ በፈረንጆች 2015 በማሌዥያ ኳላላምፑር በተካሄደው 128ኛው አይኦሲ ስብሰባ ላይ አልማቲን በአራት ድምፅ በማሸነፍ የ2022 የክረምት ኦሎምፒክ አዘጋጅ ከተማ ሆና መመረጧ የሚታወስ ነው።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.