Fana: At a Speed of Life!

ቻይና የውጭ ጣልቃ ገብነትን አጥብቃ እንደምትቀወም የሀገሪቱ ኮሚኒስት ፓርቲ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ቻይና የውጭ ጣልቃ ገብነትን አጥብቃ እንደምተቃዎም የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ በድጋሜ አስታወቀ።
በፕሬዚደንት ዥ ዥፒንግ የሚመራዉ የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ 19 ኛውን የማዕከላዊ ኮሚቴ ስድስተኛ ጠቅላላ ጉባኤ በዋና ከተማዋ ቤጂንግ ከህዳር 8 እስከ 11 ባሉት ጊዜያት አካሄዷል፤ የተለያዩ ዉሳኔዎችንም አስተላልፏል፡፡
የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ ባደረገዉ ውይይትና ባስተላለፈው ውሳኔ የቻይና የፖለቲካ ርዮተ ዓለም የሆነው በራሷ መንገድ የሚመራ የቻይና ህብረተሰባዊነት ፍልስፍና አገሪቱን ወደ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ ማሸጋሩ ተገልጿል።
የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ህዝቡ በራስ የመተማመን መንፈስን በማጎልበት እና ከዚህ ቀደም የተገኙ ተሞክሮዎችን መሰረት በማድረግ አዳዲስ ፈጠራዎችን በማጎልበት ረገድ በህብረተሰባዊነት ትልቅ ስኬት ማስመዝገቡን አብራርቷል።
በዚህ ወቅት ፓርቲው ባስተላለፋቸዉ የተለያዩ ፖለቲካዊ ዉሳኔዎች ቻይና የውጭ ጣልቃ ገብነትን አጥብቃ እንደምትቃወም አረጋግጣለች።
የውጭ ጉዳይን በተመለከተ፥ ቻይና ከሁሉም ሀገራት ጋር የሁለትዮሽ ብሄራዊ ጥቅምን ባስቀደመ መልኩ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን እያጠናከረች መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ቻይና በምታደርገው አለማቀፋዊ የዲፕሎማሲ ጥረት የምዕራባዉያንን ተገቢ ያልሆነ ጫና እና በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባትን የሰበረች ሲሆን፥ በአለም አቀፍ ደረጃ የተፈጠሩ ቀውሶችን ለማረጋጋት ከፍተኛ ጥረት ማድረጓ ተገልጿል፡፡
ማዕከላዊ ኮሚቴው በ2022 ሁለተኛ አጋማሽ 20ኛውን ብሄራዊ ኮንግረስ በቤጂንግ እንደሚያካሂድ በስብሰባው የወሰነ ሲሆን ፥ዘመናዊ ህብረተሰባዊት ሀገር በሁሉም ረገድ ለመፍጠር እና የሁለተኛውን ክፍለ ዘመን ግብ እውን ለማድረግ ፓርቲው በትኩረት እንደሚሰራ ዉሳኔ ላይ መድረሱን ከቻይና ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.