Fana: At a Speed of Life!

ቻይና የ2020 የኢኮኖሚ ዕድገት ግብን እንደማታስቀምጥ አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቻይና አመታዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ግብን እንደማታስቀምጥ አስታወቀች።

የኮሮና ቫይረስ በኢኮኖሚ ላይ ካስከተለው ተፅእኖ ጋር በተያያዘ ቻይና ከፈረንጆቹ 1990 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አመታዊ አጠቃላይ የሃገር ውስጥ ምርት እድገት ግብ እንደማይኖራት አስታውቃለች።

ይህ ይፋ የተደረገውም በሀገሪቱ አመታዊ የፓርላማ ስብሰባ መጀመሪያ ላይ ነው።

የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኬ ያንግም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በዓለም ምጣኔ ሃብትና የንግድ እንቅስቃሴ ላይ በተጋረጠው አደጋ ምክንያት አንዳንድ ጉዳዮች ላይ እርግጠኛ መሆን አይቻልም ብለዋል።

የሃገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እድገት ከአመት በፊት ከነበረው የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አንጻር በ6 ነጥብ 8 በመቶ ቀንሷል።

በቻይና እስካሁን 84 ሺህ79 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ 4 ሺህ 638 የሚሆኑት ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል።

ምንጭ፦ አልጀዚራ እና ቢቢሲ

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.