Fana: At a Speed of Life!

ቻይና 800 ሺህ ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ለኢትዮጵያ ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)ቻይና ለኢትዮጵያ ያደረገችው የ800 ሺህ ዶዝ ሲኖፋርም የኮቪድ -19 ክትባት ዛሬ አዲስ አበባ ገብቷል።

ድጋፉ ቻይና ለኢትዮጵያ ለመስጠት ያቀደችው የ2 ሚሊየን ዶዝ ክትባት አካል ነው ተብሏል።

የክትባት ድጋፉን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ከሆኑት ዣዎ ዢዩዋን ተረክበዋል።

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣዎ ዢዩዋን ክትባቱ በተለይም የመንግስት ሰራተኞችና ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመድረስ እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

ቻይና ወረርሽኙን ለመከላከል በየጊዜው ድጋፍ ስታደርግ መቆየቷ ገልፀው ቀሪውን የክትባት ዶዝም በአፋጣኝ ድጋፍ እንደምታደርግ ተናግረዋል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ኢትዮጵያ የወረርሽኙን ጫና ለመቀነስ የምታደርገውን ጥረት ቻይና ስትደግፍ መቆየቷን ገልፀው ይህ የክትባት ድጋፍም ሀገሪቱ በርካታ ዜጎችን በክትባት የመድረስ የያዘችውን እቅድ ያግዛል ብለዋል።

በኢትዮጵያ እስካሁን 4 ሚሊዮን የሚደርሱ ዜጎች የኮቪድ ክትባት መውሰዳቸው መገለፁን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

ሆኖም አሁንም ወረርሽኙ እያደረሰ ያለው ጫና ከፍተኛ በመሆኑ ተፅዕኖውን ለመቀነስ ክትባቱን በስፋት ለዜጎች ማድረስ ይጠበቃል ተብሏል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.