Fana: At a Speed of Life!

ኅብረት ሥራ ኤጀንሲና አልፋ ዩኒቨርሲቲ ለህልውና ዘመቻው ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ እና አልፋ ዩኒቨርሲቲ ለመከላከያ ሠራዊት የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ፡፡
የፌዴራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ለሠራዊቱ ከ2 ሚሊየን 800 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ ሲያደርግ÷ አልፋ ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ የ100 ሺህ ብር ድጋፍ አድርጓል።
የህወሓት የሽብር ቡድን የከፈተውን ጥቃት በመመከት የሀገርን ህልውና ለማዳን በሚደረገው ዘመቻ ተቋማቱ የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልጸዋል፡፡
አሁን ያደረጉት ድጋፍም ሀገርን ለማፍረስ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው እና በዜጎች ላይም ኢ ሰብአዊ ድርጊት እየፈፀመ የሚገኘውን የሽብር ቡድን ለመከላከል ከፍተኛ የሕይወት መሥዋዕትነት እየከፈለ ከሚገኘው ሠራዊት ጎን መሆናቸውን ለማሳየት መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
ድጋፋቸውንም አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ድጋፉ አሁንም ሕዝባችን ከሠራዊቱ ጎን ደጀን ሆኖ መቆሙን ያረጋገጠበት ነው ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ማርታ ሉጂ ተናግረዋል፡፡
በተለያዩ መንገዶች ለሠራዊቱ የሚደረገው ድጋፍም በግንባር እየተፋለመ ላለው ሠራዊቱ የሽብር ቡድኑን ለማስወገድ ትልቅ የሞራል ስንቅ መሆኑንም ገልጸዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.