Fana: At a Speed of Life!

ነገ ለሚካሔደው ሀገራዊ ምርጫ በደቡብ ወሎ ዞን በደሴና ደሴ ዙሪያ አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ነገ ለሚካሔደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በደቡብ ወሎ ዞን በደሴና ደሴ ዙሪያ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በተንቀሳቀሰባቸው በደሴ ከተማ፣ በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ዙሪያ ወረዳዎች ማለትም በገልሻ፣በጉጉፍቱና በጠባሲት የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁሶቹ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጧል።
የየምርጫ ጣቢያዎቹ ሀላፊዎችም የድንኳን ተከላን ጨምሮ የመጨረሻው የድምጽ አሰጣጥ ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን ተናግረዋል።
የየአካባቢዎቹ ነዋሪዎች በበኩላቸው ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን ለማድረግ ከጸጥታ መዋቅር ጋር እየሰሩ መሆኑንና ለምርጫ መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።
በለይኩን ዓለም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.