Fana: At a Speed of Life!

ነፃ የወጡ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስተባብር ቡድን ተቋቋመ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአሸባሪው ቡድን ነፃ የወጡ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስተባብር ቡድን ማቋቋሙን የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡
የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ነፃ የወጡ አካባቢዎችን እየተከታተለ የጥገናና የወደሙ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን መልሶ በመገንባት ከተሞች በፍጥነት የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስተባብር ቡድን ማቋቋሙን አስታውቋል።
ከነገ ጀምሮ አንድ ቡድን ወደ ፍላቂት እና ጋሸና መስመር ወዳሉ ከተሞች የሚንቀሳቀስ መሆኑን የዲስትሪቢዩሽን ሲስተም ቴክኒካል ድጋፍ ኃላፊ አቶ ሽመላሽ ግርማው ተናግረዋል፡፡
አሸባሪው ቡድን በወልድያ ዲስትሪክት ስር የሚገኙ 13 አገልግሎት መስጫ ማእከላትን ሙሉ በሙሉ፣ በደሴ ዲስትሪክት ስር የሚገኙ 23 አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን ሙሉ በሙሉ እንዲሁም በደብረብርሃን ዲስትሪክቶች ስር የሚገኙ 9 አገልግሎት መስጫ ማእከላት ላይ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲቋረጥ እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ የመሰረተ ልማት ጉዳትና ውድመት ማድረሱን የክልሉ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገልጿል፡፡
አሸባሪው ቡድን ደቡብ ጎንደር ዞን ገብቶ በነበረበት ወቅት ያወደመውን የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት አካባቢው ነፃ መውጣቱን በመንግስት እንደተገለፀ፥ የክልሉ ሠራተኞች ባደረጉት ከፍተኛ ርብርብ ወዲያውኑ መልሶ የማገናኘት ስራ በመስራት አካባቢው የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኝ መድረጉ ተመላክቷል፡፡
በደቡብ ጎንደር ዞን በሚገኙ 2 አገልግሎት መስጫ ማዕከላቶችና በስራቸው በሚገኙ ሳተላይ ጣቢያዎች ብቻ 2 ሚሊየን 447 ሺህ 747 ብር የሚገመት ውድመት መድረሱን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.