Fana: At a Speed of Life!

ናሳ በማርስ ላይ ሮቦት በተሳካ ሁኔታ አሳረፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ተቋም (ናሳ) በማርስ ላይ ሮቦት በተሳካ ሁኔታ ማሳረፉ ተገልጿል፡፡

ተቋሙ ጀዜሮ ተብሎ በሚጠራው የፕላኔቷ ወገብ አካባቢ በሚገኘው ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ሮቦቷን በተሳካ ሁኔታ ማሰረፉ ተገልጿል፡፡

የተልዕኮው ምክትል ሥራ አስኪያጅ ማት ዋላስ “ የጠፈር መንኮራኩሩ በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል” ብለዋል፡፡

በካሊፎርኒያ ውስጥ በናሳ የሚገኙ መሐንዲሶች ሮቦቷ ማርስ ላይ ማረፏን ካረጋገጡ በኋላ ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በትዊተር ገጻቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ባለ ስድስት ጎማዋ ሮቦት በፕላኔቷ ላይ የቆዩ ማስረጃዎችን በመሰብሰብ ከዚህ ቀደም በፕላኔቷ ላይ ህይወት ያለው ፍጡር ስለመኖር አለመኖሩ ማረጋገጫ ትሰጣለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ለዚህም በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት በአካባቢው አለታማ ድንጋዮች ቁፋሮ ታካሂዳለችም ነው የተባለው፡፡

ጄዜሮ በቢሊየኖች ከሚቆጠሩ ዓመታት በፊት ግዙፍ ሐይቅ እንደነበረበት ይነገራል፡፡

ይህም በአካባቢው ህይወት ያለው ፍጡር ሊኖር ይችላል የሚለውን መላ ምት አጠናክሮታል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.