Fana: At a Speed of Life!

ናሳ በጸሐይ ዙሪያ መረጃ የምታሰባስብ አዲስ መንኮራኩር ወደ ህዋ ሊልክ ነው  

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ተቋም (ናሳ) በጸሐይ ዙሪያ መረጃ የምታሰባስብ አዲስ መንኮራኩር ወደ ህዋ ሊልክ መሆኑን አስታውቋል።

በናሳ እና በአውሮፓ ጠፈር ምርምር ተቋም በጋራ ወደ ህዋ የምታላከው መንኮራኩር የጸሃይን ሰሜን እና ደቡብ ዋልታ የሚያሳይ የመጀመሪያ ምስል ወደ መሬት እንደምትልክ ይጠበቃል።

ከዚህ ባለፈም በዋልታዎቹ ዙሪያ የሚገኙ የተለያዩ አዳዲስ መረጃዎችን ታሰባስባለችም ነው የተባለው።

መረጃው የዘርፉ ተመራማሪዎች በጸሃይ ዙሪያ የሚከሰቱ ማዕበሎች ከመከሰታቸው በፊት ቀድመው በጥሩ ሁኔታ እንዲተነብዩ ያስችላቸዋል ነው የተባለው ።

መንኮራኩሯ የፊታችን የካቲት ወር ላይ ወደ ህዋ የምታላክ ሲሆን፥ ከጸሓይ በ26 ሚሊየን ማይል ርቀት ላይ እንደምትሽከረከርም ነው የተገለጸው።

ምንጭ፡- ደይሊ ሜይል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.