Fana: At a Speed of Life!

ናሳ የሰው ልጅ ሊኖርበት የሚችል አዲስ ፕላኔት ማግኘቱን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 29 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው የጠፈርና የህዋ ምርምር ተቋም (ናሳ) የሰው ልጅ ሊኖርበት የሚችል አዲስ ፕላኔት ማግኘቱን አስታውቋል።

ቲ ኦ አይ 700 ዲ የተሰኘው ፕላኔት በመጠን ከምንኖርባት መሬት ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው ናሳ አስታውቋል።

አዲሱ ፕላኔት ከምቹነት አንጻር ለሰው ልጅ ተስማሚ የሚባል የአየር ንብረት እንዳለውም ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈም ምድር ከፀሐይ ከምታገኘው ኃይል 86 በመቶውን ይቀበላል ነው የተባለው።

ፕላኔቱ ከምድር በ100 የብርሃን አመታት እንደሚርቅም ነው የህዋ ሳይንስ ተመራማሪዎች የገለጹት።

ከዚህ በተጨማሪም ከከዋክብት ብዙም የማይርቅና ብዙም የማይቀርብ መሆኑ የሚኖረው ሙቀት ፕላኔቱ ፈሳሽ ውሃ እንዲይዝ እንደሚያስችለውም አስረድተዋል።

ተመራማሪዎቹ በፕላኔቱ አጠቃላይ አፈጣጠርና ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ተጨማሪ ጥናትና ምርምር እናደርጋለንም ብለዋል።

ምንጭ፦ ሲ ጂ ቲኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.