Fana: At a Speed of Life!

ናሳ የስምንት ሃገራትን የጠፈር ምርምር ጥምረት ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ የጠፈር ምርምር ማዕከል (ናሳ) ”አርቴሚስ ስምምነት” በተባለ ማዕቀፍ የተመሰረት የስምንት ሃገራትን የጠፈር ምርምር ጥምረት ይፋ አድርጓል፡፡

ስምምነቱ ለወደፊቱ በጨረቃ እና ሌሎች የጠፈር አካባቢዎች ለሚደረገው ቅኝት መርህ ደረጃ ደንቦችን ባካተተ መልኩ የተፈረመ ነው ተብሏል፡፡

አውስትራሊያ፣ ካናዳ ፣ ጣልያን፣ ጃፓን፣ ሉክዘምበርግ፣ የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች፣ ብሪታንያ እና አሜሪካ መስራች ሃገራት በመሆን ስምምነቱን ተቀላቅለዋል፡፡

በስምምነቱ መሰረትም በፈረንጆቹ 2024 የሰውን ልጅ ወደ ጨረቃ ለመላክ ያለመ መሆኑም ነው የተነገረው፡፡

ስምምነቱ በታሪክ እጅግ በጣም ሰፊ እና የተለያዩ አካላትን ያካተተ የጠፈር ምርምር መርሃግብር እንደሚሆንም ተገልጿል፡፡

ናሳ ጨረቃ ላይ መኖሪያ ለመገንባት ዓለም አቀፍ ጥምረቶች አስፈላጊ መሆናቸውን አፅንዖት ሰጥቶ ይገልጻል፡፡

ምንጭ፡- ሲ.ጂ.ቲ.ኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.