Fana: At a Speed of Life!

ኔዳምኮ ካፒታል በቴክኖሎጂው ዘርፍ 10 ሺህ ወጣቶችን ማሰልጠንና ወደ ስራ የማስገባት ፍላጎት እንዳለው ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 29 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኔዳምኮ ካፒታል የተሰኘው የኔዘርላንድስ ቴክኖሎጂ ኩባንያ በኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዘርፍ 10 ሺህ ወጣቶችን ማሰልጠንና ወደ ስራ የማስገባት ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማሪያም ከኔዳምኮ ካፒታል ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በዚህ ወቅትም ኩባንያው በተለይ በክላውድ እና የስልክ (ሞባይል) ክፍያ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ 10 ሺህ ወጣቶችን ማሰልጠን እና ወደ ስራ ለማስገባት ያለውን ዝግጁነት ገልጿል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለኔዳምኮ ካፒታል እቅድ ስኬታማነት በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

ኔዳምኮ ካፒታል በ55 ሀገራት በሶፍትዌር፣ በጤና አጠባበቅ እና በመረጃ ቴክኖሎጂ ዘርፎች ተሰማርቶ ይገኛል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.