Fana: At a Speed of Life!

አላግባብ የሲሚንቶ ዋጋ መጨመር የግንባታ ኢንዱስትሪውን እንደሚጎዳ የንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 21 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አላግባብ የሲሚንቶ ዋጋ መጨመር የግንባታ ኢንዱስትሪውን እንደሚጎዳ የንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዘርፉ ከተሰማሩ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

በውይይቱም ሲሚንቶን ከሌሎች የፍጆታ ዕቃዎች እኩል በትኩረት እንደሚያየው የንግድና የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ተናግረዋል።

እንዲሁም በአንዳንድ የሀገሪቱ ከተሞች በጥቁር ገበያ አንድ ኩንታል ሲሚንቶ እሰከ 650 መቶ ብር መሸጡ አግባብ እንዳልሆነ በመድረኩ ተነሰቷል ።

እስካሁንም በመድረኩ የአቅርቦት ችግር እንደሌለ የተነሳ ሲሆን፥ ህግ ወጥ ደላሎች በዋነኛነት ለዋጋ መጨመሩ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አላቸው ተብሏል።

በሌላ በኩል የትራንስፖርት ችግር እና ባለፉት ወራት ሁሉም የሲሚንቱ ፋብሪካዎች 50 በመቶ ቀንሰው የመብራት ሃይል መጠቀማቸው ለዋጋ መጨመር ሌላኛው ምክንያት ነበር ተብሏል ።

በሲሳይ ጌትነት

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.