Fana: At a Speed of Life!

አልሸባብ አሜሪካና ኬንያ በሚጠቀሙበት ወታደራዊ ጣቢያ ላይ ጥቃት ፈፀመ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው የሽብር ቡድን አልሸባብ በደቡብ ምስራቅ ኬንያ አሜሪካና ኬንያ በጋራ በሚጠቀሙበት ወታደራዊ ጣቢያ ላይ ጥቃት ፈፀመ።

አልሸባብ ጥቃቱን የፈፀመው በታዋቂው የባህር ዳርቻ ላሙ በሚገኘው ወታዳራዊ ጣቢያ ላይ መሆኑን የኬንያ ጦር አስታውቋል፡፡

ጥቃቱን ተከትሎም በወታደራዊ ጣቢያው የነበሩ ወታደሮች እንዲወጡ መደረጉን የኬንያ መከላከያ ሀይል ገልጿል፡፡

በአካባቢው የነበሩ የአይን እማኞች ጥቃቱ በተፈፀመበት ወታዳራዊ ጣቢያ የተኩስ ልውውጥ እና ከካምፑ የሚወጣ ጭስ ረፋድ ላይ መመልከታቸውን ገልፀዋል፡፡

የኬንያ መከላከያ ኃይል ቃል አቀባይ እንደገለጹት አልሸባብ ጥቃቱን ሲያደርስ በወሰዱት የአጸፋ እርምጃ አራት የቡድኑ አባላት ተገድለዋል።

የአልሸባብ ወታደሮች በአሜሪካና በኬንያ ወታደሮች ጥቅም ላይ የሚውለውን ወታደራዊ ሰፈር ለመቆጣጠር በማሰብ ጥቃቱን እንደሰነዘሩ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

ከጥቃቱ ጋር ተያይዞ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ቦቴዎች በመፈንዳታቸው ከባድ ፍንዳታና ጭስ አካባቢውን እንደሞላው ተገልጸል።

በጥቃቱ በአሜሪካ እና በኬንያ ወታደሮች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን  ሁለት አውሮፕላኖች ፣ ሁለት የአሜሪካ ሄሊኮፕተሮች እና በርካታ ተሽከርካሪዎች  ወድመዋል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት  ታጣቂ ቡድኑ በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ  ባደረሰው የቦንብ ፍንዳታ 80 ያህል ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል ፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.