Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካውያን በሰላማዊ የስልጣን ሸግግር ማመን አለባቸው- ቦሪስ ጆንሰን

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አሜሪካውያን ኮንግረስ ካፒቶል ሂል ውስጥ በሀይል በመግባታቸው እየተወቀሱ ነው።

ሰዎቹ ካፒቶል ሂል ሰብረው ሲገቡ የህግ አውጪዎች ስነ-ስርአት የሆነው ኢሌክቶራል ቮት እየተቆጠረ ነበር።

በሂደቱም የድምፅ ቆጠራ ተጠናቆ ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ማሸነፋቸውን ለማወጅ በዝግጅት ላይ ነበሩ ተብሏል።

ሁከት የፈጠሩ ሰዎች የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተሰርቋል ብለው የሚያምኑ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች ናቸው ነው የተባለው።

የምክር ቤቱ አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ እና የኮንግረስ አባላት ለደህንነታቸው ሲባል ወደ ሌላ ቦታ መወሰዳቸውም ተነግሯል።

የፀጥታ አካላት ብዙ ጉደት ሳይደርስ ችግሩን ለመቆጣጠር ተንቀሳቅሰዋል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሁከቱ ተገቢ ያለመሆኑን የገለጹ ሲሆን ቀደም ሲል ለደጋፊዎቹ የምርጫውን ዉጤት እንደማይቀበሉ ማሳወቃቸው አይዘነጋም።

ትራምፕ ደጋፊዎቻቸው ናቸው ለተባሉ ሰዎች በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ወደ ቤታችሁ ግቡ ብለዋል።

የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በትዊተር ገጻቸው ጉዳዩን በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት ድርጊቱ የታላቋን ሀገር የአሜሪካን ክብር የማይመጥን አሳፋሪ ተግባር ሲሉ ገልጸውታል።

አሜሪካውያን በሰላማዊ የስልጣን ሸግግር ማመን እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

ምንጭ፦ቢቢሲ፥ ሲ ኤን ኤንና አልጀዚራ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.