Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ሙሉ ለሙሉ ክትባት የወሰዱ ዜጎቿ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ሳይጠቀሙ እንዲንቀሳቀሱ ፈቀደች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ሙሉ ለሙሉ የኮሮና ቫይረስ ክትባት የወሰዱ ዜጎች እጅግ በርካታ ሰው ከተገኘበት ቦታ ውጭ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ሳይጠቀሙ እንዲንቀሳቀሱ ፈቃድ ሰጠች።

የአሜሪካ በሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማዕከል ያወጣው መመሪያ ሙሉ ለሙሉ የተከተቡ አሜሪካውያን የአፍ እና አፍንጫ  መሸፈኛ ጭምብል ሳይጠቀሙ የእግር ጉዞ ማድረግ፣ ብስክሌት መንዳት ፣ ማህበራዊ ህይወት ላይ መሳተፍ እና ካፌና ሬስቶራንት መጠቀም  እንደሚችሉ አስታውቋል።

ውሳኔው መጠነኛ የሰው መጨናነቅ በሚስተዋልባቸው አካባቢዎች የሚተገበር ሲሆን፥ ሰው በብዛት በሚስተዋልባቸው ስፍራዎች ግን ጭምብል እንዲጠቀሙ ያዛል፡፡

ይህ ውሳኔም ካለፈው የፈረንጆቹ ዓመት  ጀምሮ ማዕከሉ ዜጎች የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲቀጠሙ ሲያቀርብ የነበረውን ምክር እንዲቀይር አድርጓል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ  ባይደን  ክትባት የወሰዱ አሜሪካውያን ከጓደኞቻቸው ጋር መሰባሰብ እና በፓርኮች ምግብ መመገብ እንደሚችሉ ነው ይፋ ያደረጉት።

ጆ ባይደን ሰኔ 4 ቀን በሚከበረው የነፃነት ቀን አሜሪካውያንን ለመደበኛ የተቃረበ ህይወት መኖር እንዲጀምሩ ለማድረግ እና አሜሪካ  ከኮሮና ቫይረስ ነፃ እንድትሆን ግብ አስቀምጠዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.