Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ በሶማሊያ በሸመቁ የአልሸባብ አሸባሪዎች ላይ የአየር ጥቃት ፈፀመች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በሶማሊያ በሸመቁ የአልሸባብ አሸባሪዎች ላይ የአየር ጥቃት ፈፀመች፡፡

የአሜሪካ የመከላከያ ዕዝ ማዕከል ፔንታጎን እንዳስታወቀው÷ የአሜሪካ ኃይሎች የአየር ላይ ጥቃቱን የፈፀሙት ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት አለው በተባለው የአልሸባብ ቡድን ላይ ነው፡፡

የፔንታጎን ቃል አቀባይ ሲንቲያ ኪንግ እንዳሉት፥ እርምጃው የተወሰደው ጋልካዮ በምትባል አካባቢ ባሉ የአልሸባብ አሸባሪዎች ላይ ነው፡፡

ጥቃቱ የተፈጸመው የሀገሪቷ መንግስት ከአሜሪካ እና ከአፍሪካ እዝ ኃይል ጋር በመተባበር እንደሆነም ታውቋል፡፡
ቅዳሜ በደቡብ ሶማሊያ ግዛት በመካከለኛው ጁባ አካባቢ የምትገኝ ጂሊብ በምትባለው ስፍራ በተወሰደው እርምጃ የ52 የአልሸባብ ተዋጊዎች ሕይወት እንዳለፈ ይታወሳል፡፡
ምንጭ ÷ሲጂቲኤን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.