Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ በቻይና ቼንግዱ ከተማ የሚገኘውን ቆንስላዋን ዘጋች

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በቻይና ቼንግዱ ከተማ የሚገኘውን ቆንስላዋን ዘግታ ወጣች፡፡

ቻይና ባለፈው ሳምንት አሜሪካ በቼንግዱ የሚገኘው ቆንስላዋን እንድትዘጋ ትዕዛዝ መስጠቷ ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎም አሜሪካ ቆንስላዋን በዛሬው እለት ዘግታ ወጥታለች፡፡

ከቻይና ውሳኔ ቀደም ብሎ አሜሪካ በሂውስተን የሚገኘው የቻይና ቆንስላ እንዲዘጋ ትዕዛዝ ሰጥታ ነበር፡፡

ቻይናም ለአሜሪካ እርምጃ አፀፋዊ ምላሽ በመስጠት ነበር የቼንግዱው የአሜሪካ ቆንስላ እንዲዘጋ ያዘዘችው፡፡

የቼንግዱ የአሜሪካ ቆንስላ ካለው ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ አንጻር ለአሜሪካ ወሳኝ መሆኑ ይነገራል፡፡

ዋሽንግተን በቆንስላው አማካኝነት ቲቤትን ጨምሮ ቻይና ግዛቴ በምትላቸው አካባቢዎች የሚካሄዱ እንቅስቃሴዎችን የተመለከቱ መረጃዎችን ታሰባስብበታለች፡፡

ምንጭ፣ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.