Fana: At a Speed of Life!

የአሜሪካን ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ሰልፍ ነገ በዋሺንግተን ዲሲ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ዓቀፉ #በቃ ንቅናቄ አካል የሆነው ሰላማዊ ሰልፍ በኢትዮጵያውያን አቆጣጣር በነገው ዕለት ከምሽቱ ሶስት ሰአት በነጩ ቤተ መንግሥት ፊት ለፊት እንደሚካሄድ የሰላምና አንድነት ማህበር የዋሺንግተን ዲሲ ግብረ ሃይል አሳወቀ፡፡
ሰላማዊ ሰልፉ የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያና ኤርትራ ላይ እየተከተለ ያለውን የተሳተተ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ እንዲያስተክልና ጣልቃ ገብነቱን እንዲያቆም በሰልፈኞቹ መልዕክት እንደሚተላለፍ ተገልጿል።
ሰልፈኞቹ በአሸባሪው የሕወሓት ቡድን በኢትዮጵያ ላይ የከፈተውን ጥቃት የሚያውግዙና ለኢትዮጵያ አጋርነታቸውን የሚያሳዩባቸው መፈክሮች ያሰማሉ ነው የተባለው።
የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ ጣልቃ ገብነቱን እንዲያቆም ጫና ለማድረግ ሰላማዊ ሰልፉ በዋሺንግተን ዲሲ በየሳምንቱ እንደሚካሄድ የሰላምና አንድነት ማህበር የዋሺንግተን ዲሲ ግብረ ሃይል አሳውቆኛል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ነገ በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ የሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ሰላምና አንድነት ማህበር የዋሺንግተን ዲሲ ግብረ ሃይል ከ #በቃ ዘመቻ አስተባባሪዎች፣ ከተለያዩ ተቋሞችና አገር ወዳዶች ጋር በመተባባር ያዘጋጀው ነው።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.