Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ በኮሮና ቫይረስ አደጋ ላይ የወደቀውን ኢኮኖሚዋን ለመደገፍ 2 ትሪሊየን ዶላር በጀት አፀደቀች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካ ምክር ቤት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት አደጋ ላይ የቀደቀውን ኢኮኖሚ ለመደገፍ 2 ትሪሊየን ዶላር በጀት አፀደቀ።

የፀደቀው በጀት የእርዳታ ድርጅቶችን፣ የንግድ ተቋማትን እና የጤና ስርዓቱን ለመደገፍ ይውላል ተብሏል።

ይህንን ፓኬጅ ለማፅደቅ  ከምክር ቤቱ አባላት ጋር ከፍተኛ ድርድር ሲደረግ መቆየቱ ነው የተነገረው።

በአሜሪካ 55 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 800 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው ማለፉ ተጠቁሟል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.