Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ በየመን የአልቃይዳን መሪ መግደሏን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አሜሪካ በየመን የአልቃይዳ መሪ ቃሲም አል ራይሚን መግደሏን አስታወቀች።

ከነጩ ቤተ መንግስት የወጣ መግለጫ አል ራይሚ በአሜሪካ መከላከያ በድሮን በተፈጸመበት ጥቃት መገደሉን ያመላክታል።

ቃሲም አል ራይሚ ከፈረንጆቹ 2015 ጀምሮ በአረቢያን የባህር ሰርጥ የአልቃይዳ መሪ በአሜሪካ ከተገደለ በኋላ ቡድኑን ሲመራ ቆይቷል።

አል ራይሚ ከፈረንጆቹ 2000 ጀምሮ በአሜሪካ ጥቅምና ፍላጎቶች ላይ ከተፈጸሙ ጥቃቶች ጀርባ እጁ እንዳለበት ይነገራል።

የአል ራይሚ የመገደል ዜና በወሩ ማብቂያ አካባቢ ሲነገር ቢቆይም ቡድኑ ግን የእርሱን የድምጽ መልዕክት ከአራት ቀን በፊት አሰምቷል።

በየመን ያለው ፖለቲካዊ ቀውስ አል ቃይዳ በአካባቢው እንዲሰራፋ እድል ፈጥሮለታል ነው የተባለው።

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.