Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ኢራንን ማገዝ ከፈለገች የጣለችውን ማዕቀብ ማንሳት እንዳለባት ፕሬዚዳንት ሃሰን ሮሃኒ ተናገሩ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ኢራን ኮሮና ቫይረስን ለመዋጋት የምታደርገውን ጥረት ማገዝ ከፈለገች የጣለችውን ማዕቀብ ማንሳት እንዳለባት ፕሬዚዳንት ሃሰን ሮሃኒ ተናገሩ።

ፕሬዚዳንቱ በቴሌቪዥን ባደረጉት ንግግር አሜሪካውያን ፖለቲከኞችን “ዋሾዎች” ሲሉ ገልጸዋቸዋል።

ሮሃኒ በንግግራቸው አሜሪካውያን ቴህራንን ማገዝ ከፈለጉ ድጋፍ ማቅረብ ሳይሆን በኢራን ላይ የጣሉትን ማዕቀብ ማንሳት ይገባቸዋልም ነው ያሉት።

አያይዘውም የዋሽንግተን ባለስልጣናት ይህን ማድረግ ከቻሉ ኢራንም የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን መግታት ትችላለች ብለዋል።

“በኢራንን የድፍድፍ ነዳጅ ዘይት ሽያጭ እና የገንዘብ ዝውውር ላይ ማዕቀብ ጥሎ ድጋፍ ለማድረግ መሞከር በታሪክ ትልቁ ቅጥፈት ነው” ሲሉም ተደምጠዋል።

አሜሪካ በትናንትናው እለት ቴህራን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የምታደርገውን ጥረት ለማገዝ በሚል የድጋፍ ላድርግ ጥያቄ አቅርባ በመንፈሳዊ መሪው አያቶላህ አሊ ኻሚኒ ውድቅ መደረጉ ይታወሳል።

ኢራን ከቻይና ቀጥሎ በኮሮና ቫይረስ ከተጎዱ ሃገራት መካከል አንደኛዋ ስትሆን፥ እስካሁን ከ1 ሺህ 700 በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል።

ከ21 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.