Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ በኮሮና ቫይረስ ስጋት ዓመታዊ የጋራ ወታደራዊ ልምምዳቸውን አራዘሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት በየዓመቱ የሚያካሂዱትን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ አራዝመዋል።

ዋሽንግተን እና ሴኡል ዓመታዊ የጋራ ወታደራዊ ልምምዳቸውን ያራዘሙት በሀገራቱ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ወታደሮች መገኘታቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል።

በዚህም በደቡብ ኮሪያ 23 አዳዲስ የቫይረሱ ተጠቂዎች በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ ሲገኙ፥ በደቡብ ኮሪያ ከሚገኙ የአሜሪካ ወታደሮች መካከል ደግሞ አንደኛው የቫይረሱ ተጠቂ መሆኑ ተገልጿል።

የየሃገራቱ ከፍተኛ ወታደራዊ ሃላፊዎች በሰጡት መግለጫ፥ ልምምዱ እስከ ተያዘው ዓመት አጋማሽ ድረስ ሊራዘም እንደሚችል አስታውቀዋል።

ውሳኔው በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ያለውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመግታት ታስቦ የተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በቅርቡ በቻይና ሁቤይ ግዛት ውሃን ከተማ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አሁን ላይ ወደ ተለያዩ የዓለም ሀገራት እየተስፋፋ መሆኑ ይታወቃል።

በቻይና ብቻ በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 744 ሲደርስ፥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ወደ 78 ሺህ 497 ከፍ ብሏል።

በተመሳሳይ በደቡብ ኮሪያ በቫይረሱ የ13 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፥ 1 ሺህ 595 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ መያዛቸው ነው የተገለጸው።

 

ምንጭ፥ militarytimes.com

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.