Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ የምታደርገውን ሰብዓዊ ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች-አምባሳደር ጊታ ፓሲ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሀገር ግንባታ ሂደትና ዲሞክራሲን በጸና መሰረት ላይ ለማቆም እንዲቻል እያከናወናቸው ስላሉ የለውጥ ተግባራት ላይ ሚኒስትሯ ገለጻ አድርገዋል።

በተጨማሪም በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የህግ ማስከበር ሂደቱን ተከትሎ የተከሰቱ ሰብዓዊ ድጋፍ የሚሹ ሁኔታዎችን ለመቋቋም የተወሰዱ እርምጃዎችንና እየተከናወኑ ያሉ የሰብዓዊ ድጋፍና ዜጎችን መልሶ የማቋቋም ተግባራት ላይ ማብራሪያ መስጠታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የሰብዓዊ ድጋፍን ለማዳረስ የአሜሪካን ህዝብና መንግስት ላደረጉት ላቅ ያለ ድርሻም ሚኒስትሯ አመስግነዋል።

አምባሳደር ፓሲ በበኩላቸው በኢትዮጵያ የተካሄዱ ለውጦችን ሲከታተሉ የቆዩ መሆኑን ገልጸው፤ በሀገራቸው መንግስት በኩል የሚደረገው ሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንና እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችን ለመወጣት በትብብር እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.