Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ የሴራ ንድፈ ሃሳብን ለመቀልበስ ብዙ ስራዎች ይጠበቁባታል- ባራክ ሁሴን ኦባማ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካ መከፋፈልን እና ልዩነትን የበለጠ ያስፋፋውን የሴራ ንድፈ ሃሳብ ለመቀልበስ ሀገራቸው በርካታ ስራዎች እንደሚጠብቃት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ባራክ ሁሴን ኦባማ ገለፁ።

አሜሪካ ዶናልድ ትራምፕ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው ከተመረጡ በኋላ በቀጥታ ወደ በለጠ መከፋፈል እና መለያየት መግባቷን ኦባማ ተናግረዋል።

ባራክ ሁሴን ኦባማ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ጆ ባይደን የ2020 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን ማሸነፋቸው የተከፋፈለችውን አሜሪካ ወደ አንድነት ለማምጣት የመጀመሪያው ሂደት ነው ብለዋል።

ልዩነት እና መለያየትን ለመቀልበስ ከአንድ ምርጫ በላይ እንደሚያስፈልግም የቀድሞው ፕሬዚዳንት ገልፀዋል።

አሜሪካን ወደ አንድነት ለማምጣት ውሳኔዎች ለፖለተከኞች ብቻ መተው እንደሌለባቸው የገለፁት ባራክ ሁሴን ኦባማ  መዋቅራዊ ለውጥ ማምጣት እና ህዝቡ ሌላውን ማዳመጥ እንደሚገባውም ጠቁመዋል።

የቀድሞው ፕሬዚዳንት  በተቀመጡ የጋራ እውነቶች ላይ ምን መስራት ያስፈልጋል በሚለው ጉዳይ ከመከራከር በፊት መስማማት እንደሚገባም ተናግረዋል።

ሆኖም አሁንም ትልቅ ተስፋ እንደሚታያቸው የተናገሩ ሲሆን በመጪው ትውልድ ላይ መልካም አመለካከት መመልከታቸውን አንስተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.