Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ 12 ሺህ ወታደሮቿን ከጀርመን ልታስወጣ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 22 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ 12 ሺህ ወታደሮቿን ከጀርመን ልታስወጣ መሆኑን አስታወቀች፡፡

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዋሽንግተን በጀርመን ከሚገኘው 36 ሺህ ሰራዊቷ ውስጥ 1/3 የመቀነስ እቅድ እንዳላቸው ባለፈው ወር ተናግረው ነበር፡፡

ይህን ተከትሎም 12 ሺህ የአሜሪካ ወታደሮች ከጀርመን ይወጣሉ ነው የተባለው፡፡

ከዚህ ውስጥ 5 ሺህ 400 በቀጠናው የሞስኮን ተፅዕኖ ለመቀነስ በአውሮፓ ምድር ይቆያሉም ተብሏል፡፡

የመከላከያ ሚኒስትሩ ማርክ ኤስፐር የተወሰኑት በጥቁር ባህር አካባቢ ገሚሶቹ ደግሞ በባልቲክ አካባቢ እንደሚሰፍሩ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ወደ ጣሊያን እና ቤልጂየም በቋሚነት ይሰፍራሉም ነው ያሉት፡፡

የትራምፕ ውሳኔ ጀርመን በሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) በኩል ያለባትን መዋጮ በአግባቡ አትከፍልም በሚል የተወሰነ ነው ተብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈም በንግድ አሜሪካን መጠቀሚያ አድርጋለች ከሚል የመነጨ መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ውሳኔው ግን አሜሪካ ከአጋሯ ጀርመን ጋር ያላትን ግንኙነት ያሻክረዋል ተብሎም ተሰግቷል፡፡

ምንጭ፣ ሬውተርስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.