Fana: At a Speed of Life!

አምሥት አዳዲስ ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኦርቢት የኢኖቬሽን ማጎልበቻ ማዕከል አምሥት አዳዲስ ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶችን አስመረቀ፡፡
ድርጅቶቹ በጤና፣ በትምህርትና አገልግሎት ዘርፍ ያሉ ችግሮችን የቴክኖሎጂ መፍትሄ የታሰቡ እንደሆኑ የተገለጸ ሲሆን፥ በኢኖቬሽን ማጎልበቻ ማዕከሉ 120 ሃሳቦች ተመዝግበው 15ቱ የማበልፀግ ስራ ተሰርቶላቸዋል፡፡
አምስቱ በዛሬው እለት ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅት ሆነው ተመርቀዋል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አህመዲን መሐመድ ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች ገበያውን ተቀላቅለው አለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ መንግስት ሁኔታዎችን እየፈጠረ ነው ብለዋል፡፡
የተመረቁትን ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች መንግስት ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑንም ነው ሚኒስትር ዴኤታው የተናገሩት፡፡
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ አለምፀሃይ ጳውሎስ የጤና ስርዓቱን ዲጂታል በማድረግ የአገልግሎት ጥራቱን ማሻሻል ላይ ስራ እንደሚጠይቅና የጤና ሚኒስቴርም በዚህ ላይ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሜዲኬት፣ ጤና፣ ተማሪቤት፣ ገበታና ነርድ በዛሬው እለት የተመረቁ ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች መሆናው ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
የኦርቢት ስራ አስኪያጅ ፓዚዮን ቸርነት ለጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች አቅም ለመፍጠር እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የስራ እድል፣ ችግርን ለመፍታት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ከሃሳብ ጀምሮ ካምፓኒ እስኪመሰርቱ ድረስ የቴክኒክና የገንዘብ ድጋፍ እያዳደረጉ መሆኑን ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.