Fana: At a Speed of Life!

አምረፍ ሄልዝ አፍሪካ በደብረ ብርሀን ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)አምረፍ ሄልዝ አፍሪካ አለምአቀፍ የተራድኦ ድርጅት ከሰሜን እና ደቡብ ወሎ የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ ብርሀን ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ።
ድጋፉ የምግብ ግብአት አልባሳት እና የንፅህና መጠበቂያ ሲሆን፥ ግምታዊ ዋጋው ከ 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ሚሊየን ብር በላይ መሆኑም ተገልጿል።
ድጋፉን ያስረከቡት የአምረፍ ሄልዝ አፍሪካ አለምአቀፍ የተራድኦ ድርጅት የእናቶች ህፃናት ጤና ፕሮግራም ሀላፊ አቶ ስንታየሁ አበበ፥ ድርጅቱ ሴቶችና ህፃናት ላይ በርካታ ስራዎች ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።
በአሁኑ ሰአት ሴቶች እና ህፃናት በወራሪው ቡድን ተፈናቅለው ስለሚገኙ እነሱን ለመደገፍ ያለመ መሆኑን ገልፀዉ፥በቀጣይም ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የሰሜን ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ወልደአማኑኤል ፥የአምረፍ ሄልዝ አፍሪካ አለምአቀፍ የተራድኦ ድርጅት ድጋፍ በመጠለያ የሚገኙ ሴቶች እና ህፃናትን የምግብ እና የንፅህና መጠበቂያ ችግር የሚያቃልል መሆኑን ገልፀው ፥በቀጣም መሠል ድጋፎች ተጠናክረው መቀጠል ይገባቸዋል ብለዋል።
በኤልያስ ሹምዬ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.