Fana: At a Speed of Life!

አምስት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በቄለም ወለጋ ዞን አምስት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መወሰዱንና አምስት ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
በሌላ በኩል በዞኑ ጃል ያዴሳ ለተባለ የኦነግ ሸኔ አባል በባንክ በኩል ሊላክ የነበረ 122 ሺህ 950 ብር ከተጠርጣሪው ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉን ነው የዞኑ ፖሊስ የገለፀው፡፡
በቄለም ወለጋ ዞን እነዚህ ፀረ ሰላም ኃይሎች የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በመግታት የኅብረተሰቡን ሰላም ለማረጋገጥ የኦሮሚያ ፖሊስ በትጋት እየሠራ እንደሆነ ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.