Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ከአውሮፓ ፓርላማ አባል ክሪስሶላ ዛቻሮፖሉ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤልጂየም፣ ሉክሰምበርግ እና የአውሮፓ ህብረት ተቋማት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ከአውሮፓ ፓርላማ የልማት ሐብት ኮሚቴ ምክትል ሊቀመንበር እና የጋራ የፓርላማ ልዑክ ክሪስሶላ ዛቻሮፖሉ ጋር ተወያዩ፡፡
አምባሳደሯ ከጋራ የፓርላማ ልዑክ ጋር ባደረጉት ውይይት በበርካታ አገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
እንዲሁም አምባሳደር ሂሩት በትግራይ ክልል የህግ በላይነት ለማስከበር በተደረገ ዘመቻ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የሰብአዊ ርዳታ ለማድረስ፣ በህወሃት ጁንታ ቡድን የፈራረሱ የመሰረተ-ልማቶችን መልሶ ለመገንባትና የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም የተከናወኑ ስራዎች ዙሪያ ገለፃ አድርገዋል ፡፡
ክሪስሶላ በበኩላቸው በየካቲት ወር ልዑካቸው ወደ ኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት እንዲሁም በፖለቲካ እና በኢኮኖሚ ማሻሻያ ረገድ የተመለከቱትን ለውጦች በማስታወስ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ማሻሻያ እና መረጋጋት ማስቀጠል አስፈላጊ መሆኑን ማስገንዘባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.