Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ረታ አለሙ ከሩሲያ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በእስራኤል የኢትዮጵያ  አምባሳደር አምባሳደር ረታ አለሙ  ከሩሲያ አምባሳደር ከአናቶልይ  ቪክቶሪቪ ጋር በኢትዮጵያ   ወቅታዊ ጉዳዮች  ዙሪያ ውይይት አድርገዋል ።

በዉይይቱም 6ተኛዉ ብሄራዊ ምርጫ ነፃ፣ታአማኒነት ያለዉ እንዲሁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መንግስት የዲሞክራሲ ምህዳሩን በማስፋት በቂ ዝግጅት ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም ዲሞክራሲ  እንዲሰፋ እና የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ተግባራዊ እንዲሆኑ መንግስት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል ።

አምባሳደር ረታ በትግራይ ክልል ያለዉን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ መንግስት  የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትን  አጠናክሮ መቀጠሉን ፣ተፈናቃዮችን መልሶ ማቋቋምን እና  በመልሶ ግንባታ ዙሪያ በርካታ ሥራዎች እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል ።

በታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ  ዙሪያ በኢትዮጵያ፣በሱዳን እና በግብፅ መካከል የሚካሄደው ድርድር በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ  ሁሉንም ተጠቃሚ  የሚያደርግ ስምምነት እንዲደረስ  የኢትዮጵያ ፍላጎት መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ውዝግብ  ዙሪያ  ሰላማዊ እና ዲፕሎማሲያዊ  መንገድ  በመከተል በወንድማማችነት መንፈስ ችግሮች ለመፍታት ኢትዮጵያ የምታደርገዉን ጥረት  አምባሳደር ረታ አስረድተዋል ።

አምባሳደር  አናቶሊይ በበኩላቸው  ÷ የኢትዮጵያ አንድነትእና ሉዐላዊነት  መከበር እንዳለበት የአገራቸው መንግስት አቋም መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለዉ ታሪካዊ እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር መንግታቸዉ ፍላጎት እንዳለዉ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.