Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ሽብሩ ማሞ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለኩባ ፕሬዚዳንት አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኩባ የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሽብሩ ማሞ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለኩባ ፕሬዚዳንት ሚጌል ዲያስ-ካኔል አቅርበዋል።

አምባሳደር ሽብሩ በኩባ በሚኖራቸው ቆይታ የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ እና ዘርፈ-ብዙ ወዳጅነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ጠንክረው እንደሚሰሩ የገልፀዋል።

ኢትዮጵያን ወረራ ባጋጠማት አስቸጋሪ ወቅት ኩባ ያበረከተችው አስተዋጽኦ በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ የታተመ በደምና አጥትት የተፃፈ ታሪካዊ የወዳጅነት አሻራ ነው ብለዋል አምሳደሩ።

ይህም በሁለቱ አገራት ግንኙነት ውስጥ ልዩ ሥፍራ ያለው የእውነተኛ ወዳጅነት መገለጫና ሁል ጊዜ የሚታወስ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አምባሳደሩ አያይዘውም በጤና፣ በትምህርት፣ በእውቀትና በቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፎች ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማከጠናከር እንዲሁም የሕዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ለማሳደግ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

በነዚህ በዘርፎች ኩባ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንድትቀጥል ፕሬዚዳንቱን ጠይቀዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሜጌል ዲያስ-ካኔል በበኩላቸው አምባሳደሩ በቆይታቸው የኩባ መንግስትና ተቋማት ድጋፍ እንደማይለያቸውና የሁለቱን አገራት ግንኙነት ለማሳደግ ትብብር እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡

በጤና፣ በትምህርትና በቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፎች ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንዲሸጋገር እና በዘርፉ ኩባ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ማረጋገጣቸውን ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.