Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ተሾመ የኢትዮጵያ እና ቻይና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ምሥረታን 50ኛ ዓመት አስመልክቶ የተላከ መልዕክት አደረሱ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር ተሾመ ቶጋ የኢትዮጵያ እና የቻይና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ምሥረታን 50ኛ ዓመት አስመልክቶ የተላከ መልዕክት አደረሱ፡፡
አምባሳደር ተሾመ ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂፕንግ እንዲሁም ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ የተላኩ የእንኳን አደረሰን የደስታ መግለጫ ነው ያደረሱት፡፡
መልዕክቱንም በቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተገኝተው ለአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል ው ፔንግ ማድረሳቸውን በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.