Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ሱዳን የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ሜዩኪ አዩ ዴንግ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
 
በውይይቱ ወቅትም አምባሳደር ነቢል በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ በተለይም አሸባሪው ህወሓት እየገጠመው ያለውን ሽንፈት፣ የሰብዓዊ ድጋፍን ለማዳረስ እየተደረገ ያለውን ሰፊና የተቀናጀ ጥረት እንዲሁም አንዳንድ የውጭ ኃይሎች በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር የሚያደርጉትን ጥረት በተመለከተ ለሚኒስትሩ ገለጻ አድርገውላቸዋል።
ከዚህ ባለፈም መንግሥት በቅርቡ የብሔራዊ ምክክር መድረክ ለማመቻቸት ሥራ መጀመሩንም አምባሳደሩ ገልጸዋል።
 
የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ሜዩኪ አዩ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ነጻነት ከተጫወተችው የማይተካ ሚና በተጨማሪ አሁን ላይ ለደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት አተገባበር እያበረከተች ላለው አስተዋጽኦ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።
 
በተጨማሪም አገራቸው በዚህ ወሳኝ ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን እንደምትቆም ማረጋገጣቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
 
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.